Nati luxury car rental

Nati luxury car rental

Menu

Service 

ፕራውድ የቅንጦት መኪና ኪራይ ለቅንጦትና ለማይረሱ ትዝታዎች የመኪና ኪራይ አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ ልምድ ያካበተ፣ የተገነባ ስም ያለው እና ሰፊ እውቅና የተቸረው ኩባንያ ነው፡፡

ግለሰቦች፣ የግል ኩባንያዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ እና ሌሎች በርካታ ደንበኞች ለልዩ ዝግጅቶች፣ ለሰርግ፣ ለስብሰባ፣ ለጉብኝት፣ ለዕለት ተዕለት ጉዞዎች እና ለመሳሰሉት የቅንጦት መኪና ፍላጎቶቻቸው ቢሯችንን ይጎበኛሉ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የመብራት ሃይል ባለስለጣንና መሰል የመንግስት ተቋማት፣ የበርካታ ኩባንያዎች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች፣ የውጭ ዜጎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ባለሃብቶች፣ ዲያስፖራዎች፣ ታዋቂ ሰዎች (ተወዳጅ ተዋንያን፣ ድምፃውያን፣ ቲክቶከሮች፣ ዩቲውበሮች እና አለማቀፍ ሞዴሎች ወዘተ) እንዲሁም ከሁሉም የአለማችን ክፍል የሚመጡ ቱሪስቶች የመጨረሻ ሞዴል (ፋሽን) መኪኖቻችንን ነድተው አገልግሎታችንን አድንቀው መስክረዋል፡፡ 

ከመኪኖቻችን አንዱን (ሌሞ፣ ሬንጅ ሮቨር፣ ቪ8፣ አይዲ 6፣ አይዲ 4፣ ቱክሰን፣ መርሴዲስ ወይም ሌሎች ብዙ ምርጫዎችዎን) በሹፌር ወይም ያለሹፌር ወስደው ይንዱና እውነተኛ ቅንጦት፣ ምቾትና ዘመናዊነትን በጥልቀት ያጣጥሙ፡፡


ፕራውድ የቅንጦት መኪና ኪራይ

በንጉሳዊነት ስሜት ይንዱት!

X